"እኛ ኢትዮጵያውያን ክትባትን ለማዘጋጀት አዲስ እንዳልሆንን ብዙ ማሳያዎች አሉን"።

በታሪክ አጋጣሚ በሳይንሱ አለም እጅግ አድናቆትን ስምና ዝናን ያተረፉ እውቅ ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስቶች አሉ። ለአብነት ያህል እንደ ክቡር ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ፣ እንደ ዶ/ር አክሊሉ ለማና ሌሎች በርካቶች በጉልህ ይጠቀሳሉ።
.
ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ በሙያቸው የእንስሳት ሀኪም ሲሆኑ እንዲሁም የሰው ህክምናንን ጨምሮ በማጥናት የሁለት ሞያዎች ባለቤት በመሆን አለማችን ላይ ካሉ ጥቂት የዘርፉ እውቅ ኢትዮጵያዊ ተመራማሪዎች ያደርጋቸዋል።
.
በ1935 የጣልያን ጦር ወደ ኢትዮጵያ በገባ ወቅት አብሮ ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ የሚነገረው የRinder Peste የከብቶች በሽታ ድፍን አለሙን ብሎም የሀገራችንን አርብቶ አደሮች ብዙ የሚቆጠሩ ከብቶችን በሞት አልቀው ነበር።
.
በወቅቱ በሽታው ከኃይለኝነቱ የተነሳ ታላላቅ የአለም ሀገራት የቫይረስ ተመራማሪዎች (Virologist) ቶች ሁሉ ከባድ የነበረውን ይህን በሽታ በጊዜው ብቻውን ላብራቶሪ ውስጥ ቀረ እስኪባል ድረስ "It only exists in laboratories. However, it is still a scourge in Africa, Asia and the Middle East that deprives cattle-rearing countries of billions of dollars of income".
.
ከብዙ ጥናትና ምርምር በኃላ ለበሽታው የሚሆን ክትባት በኢትዮጵያዊው ፕሮፌሰር እጅ ተገኘ። ለሀገራቸው ብሎም ለተቀረው አለም ለበሽታው ክትባት ኢትዮጵያ ታከፋፍል ጀመር። ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ ለአለም ለበሽታው ክትባት በማግኘት በማግኘት የምስራቹን ማብሰር የቻሉ ብርቱና ታታሪ ኢትዮጵያዊ ተመራማሪ ናቸው።
.
ይህም እኛ ኢትዮጵያን በወረርሽኝ መልክ ለሚከሰቱ ድንበር ተሻጋሪ በሽታዎች መድሃኒት ለማግኘት ወይም ክትባት ለማግኘት አዲስ እንዳልሆንን እና ወደፊትም መስራት እንደምንችል የፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ ታታሪነት ይያው ምስክር ነው።
.
በሽታው ከነበረው አደገኝነት የተነሳ በብዙ ክፍለ አህጉራት እንኳን ሳይቀር የብዙ ከብቶችን ህይወት የቀጠፈ የሀገራትን ኢኮኖሚያዊ አቅም የተፈታተነና የአለምን በቂ የምግብ ተደራሽነትን ጥያቄ ውስጥ የከተተ ክስተት ነበር። ይሁንና ይህን እንቆቅልሽ ለመፍታት ያልቦዘኑት ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ ይህን ትልቅ የስራ ውጤታቸውን ለአለም በማበርከት በሽታው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከአለም እንደጠፋ አድርገዋል።
.
ዛሬም ቢሆን ይህን መሰሉን ገድል በኮሮና ቫይረስ ላይ ለመፈፀም እኛ ኢትዮጵያን አንዳች የሚገድበን ነገር እንደሌለ የፕሮፌሰር ጥላሁን ተግባር ከበቂ በላይ የሆነ ህያው ማሳያ ነው። በዚህ ተግባር ልናስተውል የሚገባው ነገር ቢኖር አለምም ሆነ ኢትዮጵያ እንደ አሁኑ 21 መክዘ. የዳበረ የቴክኖሎጂ አቅም ባልነበረበት ወቅት ይህ ተግባር መፈፀሙን ነው።
.
ከኛ የሚጠበቀው ያሉንን ማበረታታት፣ ማንቃት ለበለጠ ስራ እንዲተጉ ማድረግ ነው። በመተጋገዝና በመደጋገፍ አንዱ ለአንዱ መንገድ በመሆን እኛ ኢትዮጵያውያንን ያለንን እምቅ እውቀት፣ ጥበብና ችሎታ ለአለም ማሳየት ያለብን ጊዜ ቢኖር አሁን ነው የሚል ፅኑ እምነት አለኝ።
.
በመጨረሻም ማለት የምፈልገው የኮሮና ቫይረስ ከእግዚአበሔርም ይምጣ ከሰይጣን፣ ከእንስሳትም ይምጣ ከሰው፣ ከቻይናምም ይምጣ ከሱዳን ይህን ወሬ ብሎ በማይመለከተን በየ ቡና መጠጫው፣ በሻይ በረንዳው ተሰብስበን የምናወራበት ቸልተኛለታችንን የማቆምበትና እንር በርስ የምንነታረክበት ሰዓት አይመስለኝም።
.
ይልቁኑ አንዴ ለተፈጠረው ለሆነ ነገር አብዝቶ የማይጠቅመውን አጉል ንትርክ ትተን በምንውልባቸው ስፍራዎች ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን ሰዓት ይመስለኛል። አሁን ምን እናድርግ ፤ በሽታው እንዳይስፋፋ ፤ ቤተሶቦቻችንን ብሎም ሀገራችንን እንዴት እንጠብቅ እንጂ እንዴት መጣ ከወዴት መጣ ማለት ያለብን አይመስለኝም። ይህን ለሚመለከታቸው እንተውላቸው እኛ ግን ቸልተኝነታችንን እናቁም እራሳችንን እንጠብቅ።
.
በሽታው ከየትም ይምጣ እንዴት አሁን ሀገራችንን ላይ አለ። ሁላችንም ካልተጠነቀቅን የተባልነውን የማንሰማና የማንተገብር ከሆነ የጊዜ ጊዳይ ይሆናል እንጂ ዛሬ ስለሌሎቹ እንደተረክነው የኛንም የሚተርኩ አይጠፉምና መጠንቀቅ መቆጠብ ያስፈልጋል። የሀይማኖት አባቶቻችን ያሉንን መንግስት የሚለንን መስማት ብቻ ሳይኖን መተግበር ይገባል ብዬ አምናለው።

Comments

Popular posts from this blog

World Veterinary Day 2020 promotes environmental protection