"እኛ ኢትዮጵያውያን ክትባትን ለማዘጋጀት አዲስ እንዳልሆንን ብዙ ማሳያዎች አሉን"።
በታሪክ አጋጣሚ በሳይንሱ አለም እጅግ አድናቆትን ስምና ዝናን ያተረፉ እውቅ ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስቶች አሉ። ለአብነት ያህል እንደ ክቡር ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ፣ እንደ ዶ/ር አክሊሉ ለማና ሌሎች በርካቶች በጉልህ ይጠቀሳሉ። . ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ በሙያቸው የእንስሳት ሀኪም ሲሆኑ እንዲሁም የሰው ህክምናንን ጨምሮ በማጥናት የሁለት ሞያዎች ባለቤት በመሆን አለማችን ላይ ካሉ ጥቂት የዘርፉ እውቅ ኢትዮጵያዊ ተመራማሪዎች ያደርጋቸዋል። . በ1935 የጣልያን ጦር ወደ ኢትዮጵያ በገባ ወቅት አብሮ ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ የሚነገረው የRinder Peste የከብቶች በሽታ ድፍን አለሙን ብሎም የሀገራችንን አርብቶ አደሮች ብዙ የሚቆጠሩ ከብቶችን በሞት አልቀው ነበር። . በወቅቱ በሽታው ከኃይለኝነቱ የተነሳ ታላላቅ የአለም ሀገራት የቫይረስ ተመራማሪዎች (Virologist) ቶች ሁሉ ከባድ የነበረውን ይህን በሽታ በጊዜው ብቻውን ላብራቶሪ ውስጥ ቀረ እስኪባል ድረስ "It only exists in laboratories. However, it is still a scourge in Africa, Asia and the Middle East that deprives cattle-rearing countries of billions of dollars of income". . ከብዙ ጥናትና ምርምር በኃላ ለበሽታው የሚሆን ክትባት በኢትዮጵያዊው ፕሮፌሰር እጅ ተገኘ። ለሀገራቸው ብሎም ለተቀረው አለም ለበሽታው ክትባት ኢትዮጵያ ታከፋፍል ጀመር። ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ ለአለም ለበሽታው ክትባት በማግኘት በማግኘት የምስራቹን ማብሰር የቻሉ ብርቱና ታታሪ ኢትዮጵያዊ ተመራማሪ ናቸው። . ይህም እኛ ኢትዮጵያን በወረርሽኝ መልክ ለሚከሰቱ ድንበር ተሻጋሪ በሽታዎች መድሃኒት ለማግኘት ወይም ክትባ...